Sunday, September 22, 2024
spot_img

በትግራይ የተራድኦ ሠራተኞች ፈተና መበርታቱን የመንግሥታቱ ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ለማድረስ የሚንቀሳቀሱ ሠራተኞች ፈተናቸው በርትቷል ሲል ያሳወቀው በትዊተር ገጹ ነው፡፡

እንደ ጽሕፈት ቤቱ ከሆነ ለሠራተኞቹ ፈተና ከሆኑባቸው ጉዳዮች መካከል የሰብአዊ አቅርቦቱ በሚደርስባቸው ቦታዎች ላይ የተለያዩ የታጠቁ ኃይሎች መኖራቸው ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በትግራይ ገጠራማ አካባቢዎች ይህ ችግር የጎላ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በክልሉ የሚደረገው የሰብአዊ አቅርቦት በቂ እንዳልሆነ በመግለጽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጋሮች ድጋፋቸውን እንዲያሳድጉ ሲል ጠይቋል፡፡

ከትግራይ ክልል የእርዳታ ሥራ ጋር በተገናኘ አሁንም በክልሉ ይገኛሉ የተባሉ የኤርትራ ወታደሮች የእርዳታ እህል መዝረፋቸውን የሚያመለክት ዶክመንት እንደደረሰው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በትላንትናው እለት ዘግቦ ነበር፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኮማንድ ፖስት ኃላፊ ኮማንደር ገብረመስቀል ተስፋማርያም የኤርትራ የጦር አዣዦችን ለማነጋገር ባልደረባቸውን እንደላኩ ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img