Thursday, November 21, 2024
spot_img

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ገለጹ


አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ጥር 29፣ 2014 ― የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር ‹‹የተሳካ ውይይት›› ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

የውይይቱን ዝርዝር ይፋ ያላደረጉት ከንቲባዋ፣ ‹‹ከቅድስት ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሱትን ጉዳዮችን በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተግባብተናል›› ሲሉ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬተርያት ባለፈው ረቡእ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ በእለቱ በከተማ አስተዳደሩ ኃላፊዎች እና በሲኖዶሱ መካከል ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ›› ስብሰባው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ቅዱስ ሲኖዶሱ የከተማ አስተዳደሩ ስላወጣው መረጃ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡  

ኋላም ውይይቱን በተመለከተ በወጡ መረጃዎች ከንቲባ አዳነች አበቤ የካቲት 4፣ 2014 በመንበረ ፓትሪያርኩ እንዲገኙ ቀጠሮ መያዙ ቢነገርም፣ በዛሬው እለት ከንቲባዋ ከአቡነ ማቲያስ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img