Sunday, September 22, 2024
spot_img

የምዕራቡን ኮሪደር ለመጠበቅ እስከ ደም ጠብታ እንደሚዋጉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥር 27፣ 2014 ― የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ኤታማጆር ሹሙ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሁመራ ግንባር የሆነውን ምዕራቡን ኮሪደር ለመጠበቅ እስከ ደም ጠብታ እንደሚዋጉ ገልጸዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁመራ አየር ማረፊያ በተካሄደው የሰሜን ምዕራብ እዝ የሜዳሊያ ሽልማትና የማዕረግ ማልበስ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ሕወሓት የምዕራቡን ኮሪደር ለማስከፈት እየተደንደረ ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል፡፡

የምዕራቡ ኮሪደር ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅንጅት እየሠሩበት ያለ ኮሪደር ነው ያሉት ፊልድ ማርሻሉ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይህን ኮሪደር ለመጠበቅ እስከ ደማችን ጠብታ ድረስ እንዋጋለን ብለዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሕወሓት ለስምንተኛ ጊዜ መሳሳቱን በመግለጽ፣ አሁንም የምዕራቡን ኮሪደር ለማስከፈትና ለዘጠነኛ ጊዜ ለመሳሳት እየተንደረደረ እንደሆነ መግለጻቸውም ተመላክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img