Sunday, November 24, 2024
spot_img

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ‹የትግራይ ኃይል› ሲል የጠራው ቡድን ለአፋር ሕዝብ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ሳይደርስ የሚደረግ ድርድር እንደ አገራዊ ክሕደት የሚቆጠር ነው አለ


አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥር 20፣ 2014 ― የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ‹የትግራይ ኃይል› ሲል የጠራው ቡድን ለአፋር ሕዝብ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ሳይደርስ የሚደረግ ድርድር እንደ አገራዊ ክሕደት የሚቆጠር ነው ሲል ባወጣው መግለጫው አሳውቋል፡፡

መንግሥት የመጀመሪያውን የጦርነት ምዕራፍ አጠናቅቃለሁ ብሎ ቢያውጅም ‹‹የትግራይ ወራሪ ሃይል›› ሲል የጠራው ቡድን በሰሜን በሚያጎራብቱት የአፋር ወረዳ ቀበሌዎችን እየወረረ እንደከሚገኝ የገለጸው ፓርቲው፣ በወረራ ይዟቸዋል ካላቸው የአፋር አካባቢዎች ‹‹እስካልወጣና ከባድ መሳሪያዎቹ ለአፋር ሕዝብ ስጋት ወደ ማይሆኑበት ደረጃ እስካልወረደ እና እስኪረጋገጥ ድረስ የሚደረግ ወይንም ሊደረግ የታሰበ ድርድር ካለ የአፋር ሕዝብ ይህን አካሄድ የማይቀበል መሆኑና ‹‹እንደ ሀገራዊ ክህደት የሚቆጥር›› ነው ብሎታል፡፡

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ እንዳለው ከሆነ ከጥር 15፣ 2014 ጀምሮ ቡድኑ በከባድ መሳሪያዎች በመታገዝ እስከ 50 ሺሕ የሚገመቱ ‹‹ጀሌዎቹን ልክ እንደ አንበጣ መንጋ በማሰለፍ›› በመጋሌ፣አብአላ፣ በራህሌ፣ ኮነባ እና ኢሬብቲ ወረዳዎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ እያካሄደ ይገኛል ነው ያለው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአፋር ክልል መንግስት ‹‹የክልሉ ሕገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ እና ጠንከር ያለ ኮማንድ ፖስት እንዲያደራጅ›› ሲል ፓርቲው ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል በመንግስት መግለጫዎች ጭምር የአፋርን ችግር ችላ ለማለት ሲሞከር እያስተዋልን ነው ያለው የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ ይህን ጉዳይ ‹‹በአስቸኳይ ሊታረም ይገባል›› ብሏል፡፡

በአፋር ሕዝብ ፓርቲ በጥቃት አድራሽነት የተወነጀለው ሕወሓት፣ ከሁለት ቀናት በፊት ባሠራጨው መግለጫ፣ በአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ልዩ ፖሊስና በኤርትራ መንግሥት ይደገፋል ባለው ‹‹የቀይ ባህር አፋር ኃይል›› ሲል በጠራው ኃይል ላይ ጥቃት መክፈቱን አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img