Sunday, November 24, 2024
spot_img

ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜ የሚያሳጥር የውሳኔ ሐሳብ ተላለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥር 18 2014 ― በዛሬው ዕለት 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የሚኒስትሮች ም/ቤት፣ ከጥቅምት 23፣ 2014 ጀምሮ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ በሚመለከት በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ውሳኔውን ያሳለፈው ‹‹ሕወሃት እና ግብረ አበሮቹ›› በአገሪቱ ‹‹ህልውና እና ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ›› ላይ በመጣላቸው እንደነበር ያስታወሰው ምክር ቤቱ፣ ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ነው የተገለጸው፡፡

በመሆኑም ምክር ቤቱ የውሳኔ ሐሳቡን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img