Sunday, October 6, 2024
spot_img

የእንግሊዝ ኤምባሲ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል እና ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ያደረጉት ውይይት በትክክል አልተዘገበም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በአዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ የአገሪቱ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ከኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋር በዚህ ሳምንት ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ በሚዲያዎች የቀረበው ዘገባ እውነታውን ሙሉ ለሙሉ የማያንጸባርቅ መሆኑን በመግለጽ በውይይቱ ላይ አምባሳደሩ አንስተውታል ያላቸውን ጉዳዮች ጠቅሷል፡፡

አምባሳደሩ ከጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል ያለው ኤምባሲው፣ ጨምረውም ለግጭቱ ፖለቲካዎች መፍትሔ እንዲበጅለት እንዲሁም የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መሬት ላይ እንዲወጡ ማስገንዘባቸውንም ገልጧል፡፡

በጉዳዩ ላይ ዘገባ ያቀረቡት የመንግሥት ሚዲያዎች የትግራይ ክልልን ግጭት በተመለከተ አምባሳደሩ ‹‹የተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለሃገሪቱ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሂደትና ለቀጠናው ዙሪያ መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋፅኦ ያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል›› ማለታቸውን አስነብበው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img