Saturday, October 12, 2024
spot_img

በሳዑዲ ዐረቢያ በችግር ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያን ጋር በተገናኘ የሚሠራ ልዑክ ወደ አገሪቱ ሊያቀና መሆኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥር 12፣ 2014 ― በሳዑዲ ዐረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያንን ለመመለስ የሚሠራ ልዑክ ወደ አገሪቱ ሊያቀና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡

ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚያቀናው የልዑካን ቡድኑ ከሃማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የቪዛ እና መሰል ቅድመ ዝግጀቶች እንደተጠናቀቁ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደሚጓዝም ነው የጠቁሙት፡፡

በሳዑዲ ዐረቢያ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ በችግር ውስጥ እንደሚገኙ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ 80 ሺሕ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ እስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img