Sunday, September 22, 2024
spot_img

የባልደራስ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ

የባልደራስ ለእውነተኚ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው በይፋዊ ገጹ አሳውቋል።

የፖለቲከኞቹን ከእስር የመለቀቅ በተመለከተ ጉዳዩ በሂደት ላይ ንደሚገኝ አምባ ዲጂታል ከቀናት በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ፖለቲከኞቹን ከእስር ለማስፈታት በታኅሣሥ ወር የመጀመሪያ ቀናት ከመንግሥት የተላኩ የሀገር ሽማግሌዎች ወደ ቃሊቲ በማቅናት እስረኞቹን ለመፍታት ውሳኔ ላይ እንደተደረሰና ዝግጅትም እየተደረገ እንደሚገኝ ለእስረኞቹ ነግረዋቸው ሂደቱ ቀጥሎ በዛሬው እለት ተፈተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተያዘው ወር «የሀገራችንን ችግሮች በመፍታት ዘላቂ ሰላም እንዲሁም ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት» ያለመ ነው የተባለለት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ረቀቅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጸድቋል፡፡

አሁን ከእስር የተፈቱት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኔ 23፣ 2012 ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img