Sunday, October 6, 2024
spot_img

በደቡብ ጎንደር ዞን ለብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በደቡብ ጎንደር ዞን በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደርና በላይ ጋይንት ወረዳ የብልጽግና አባላትና ደጋፊዎች የምርጫ የድጋፍ ሰልፍ አካሄደዋል፡፡

በሠልፉ ላይ የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ፣ የክልል፣ የዞኑና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ‹‹ለውጡን በፅናት እናስቀጥላለን፣ እኛ ብልፅግናዎች መደመር መንገዳችን ብልፅግና መዳረሻችን ነው፣ በውስጣዊና ውጫዊ ጠላቶች ሳንበረከክ የክልላችንን ህዝብ ብልፅግና እናረጋግጣለን›› የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድንና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርን አብረናችሁ ነን የሚሉ መልእክቶችም ታይተዋል፡፡

የአማራ ክልል ከቀናት በፊት በአጣዬ አካባቢ የተፈጠረውን የንጹሐን ጥቃት ተከትሎ በተለያዩ ከተሞቹ ገዢውን ፓርቲ ብልጽግናን የሚያወግዙ ሰልፎችን ማስተናገዱም የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img