Sunday, October 6, 2024
spot_img

አቶ ሰማ ጥሩነህ የአማራ ክልል ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ተደርገው መሾማቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― የአማራ ክልላዊ መንግሥት አቶ ሰማ ጥሩነህን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ መሾሙ ተነግሯል፡፡

አዲሱ የሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰማ፣ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የፌዴራል እና የክልል ኃላፊነቶች ያገለገሉ መሆናቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

ከነዚህ መካከል በአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር የአንክሻ ጓግሳ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ተወካይ፣ በኢፌዴሪ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሶማሊ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አማካሪ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕስ መስተዳድር ልዩ አማካሪ እና በተለያዩ ልዩ ልዩ ኃላፊነቶች ቆይተዋል፡፡

አቶ ሰማ ጥሩነህ በመጪው ሰኔ ወር እንግሊዝ አገር ከሚገኝ ዩንቨርሲቲ በኢንተርናሽናል ቢዝነስ ትምህርት ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

ባለፉት ቀናት በሰሜን ሸዋ አካባቢ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲያስጠነቅቅ የነበረው የአማራ ክልል በትላንትናው እለት በተመሳሳይ የፖሊስ ኮሚሽሩን በአዲስ መተካቱ መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img