Sunday, September 22, 2024
spot_img

ኢዜማ የመንግሥትን ሥራዎች ይከታተላል ያለውን የትይዩ ካቢኔ ማዋቀሩን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 26 2014 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በመሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ የትይዩ ካቢኔ ማዋቀሩን አሳውቋል፡፡

አዲሱ ካቢኔ ‹‹ፓርቲው ስልጣን ላይ ካልወጣ መሪው፣ ዋና ወይም ዋና ያልሆነ የፓርላማ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እንደሚሆን›› የሚደነግገውን የፓርቲውን ሕገ ደንብ መሠረት በማድረግ የተቋቋመ ስለመሆኑ ተገልጧል፡፡

እንደ ፓርቲው መግለጫ መሪው ብርሀኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሕገ ደንቡ መሰረት የመንግስትን ሥራዎች የሚከታተሉ የትይዩ ካቢኔ አባላት አዋቅረውና መድበው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ የካቢኔ አባላቱን ግን አልዘረዘረም፡፡

ኢዜማ ያቋቋመው የትይዩ ካቢኔ አባላት ከሚከውኗው ተግባራት መካከል ረቂቅ ሕጎችን መተቸት፣ በፓርላማ ሀሳብ የሚያቀርቡት አባላትን መደገፍና ማሠልጠን፣ የእያንዳንዱን የሚንስትር መሥሪያ ቤቶች ሥራ መከታተል፣ የተፎካካሪ ፓርቲውን የልዩነት ነጥቦች በየወቅቱ ማስገንዘብ፣ መንግሥትን የሚገዳደር የፖሊሲ ንድፍ ማዘጋጀት፣ በእያንዳንዱ ዘርፍ የተሰየመት የካቢኔ ሚኒስትሮች ቡድኖቻቸውን በማዋቀርና ኃላፊነታቸውን በማከፋፈል ፓርቲውን ተፎካካሪ ማድረግ ይገኝበታል፡፡

የኢዜማ ትይዩ ካቢኔ በምንም መልኩ ‹‹የተጠባባቂ መንግስትነትና የባለአደራነት ስብስብ እንዳልሆነ እወቁልኝ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተካሄደው አገራዊ ምርጫ አራት የፓርላማ መመቀመጫ ወንበሮችን ማግኘቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ መሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ተደርገው ተሾመው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img