Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሰሜን ሸዋ ዞን ታጣቂዎች በአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተነገረ

[et_pb_section admin_label=”section”] [et_pb_row admin_label=”row”] [et_pb_column type=”4_4″][et_pb_text admin_label=”Text”]

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን ትላንት ምሽት ያልታወቁ ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሲጓዙ በነበሩ የአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተነግሯል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ቅናጢ ጫላ፣ ጥቃቱ ከምሽቱ 4 ሰአት ከ30 አካባቢ በ6 የአይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ የተፈጸመ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ በተፈጸመው ጥቃት 5 ሰዎች በጥይት መመታታቸውን ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው በኩዩ እና በደገም ወረዳዎች መካከል መሆኑንም የገለጹት ኃላፊው፣ በጥቃት አድራሾቹ ላይ የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር ክትትልና እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column] [/et_pb_row] [/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img