Monday, September 23, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ የፈቀደውን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለመሰረዝ ማቀዱ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ መንግሥት የፈቀደውን ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ ለመሰረዝ ማቀዱ ተሰምቷል፡፡

ኅብረቱ ሰሞኑን ባካሄደው ወይይት ላይ ለኤርትራ ከተፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ያልተለቀቀው ቀሪ 120 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲሰረዝ የሚል ክርክር ተነስቶበት የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ እንደተያዘለት ሪፖርተር ጋዜጣ ከኅብረቱ የተገኙ መረጃዎች ወቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት እ.ኤ.አ. በ2018 የሰላም ስምምነት አድርገው ዳግም ግንኙነት በመጀመራቸው ለኤርትራ መንግሥት የተፈቀደ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለሚያገናኘው አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ውስጥ፣ ለመጀመርያው ምዕራፍ የሚውል መጠነኛ የፋይናንስ ድጋፍ ከዓመት በፊት ለኤርትራ መንግሥት መለቀቁን መረጃው ያመለክታል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በዚህ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ የመከረው የኅብረቱ የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽን ቀሪው የፋይናንስ ድጋፍ ሊሰረዝ ይገባል በማለት በሚያቀርበው ምክንያት በኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አለመሻሻሉን የሚጠቅስ ሲሆን፣ የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ መሳተፉና ከትግራይ ክልል እንዲወጣ በአውሮፓ ኅብረትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ለመተግበር ዳተኝነት አሳይቷል የሚል ምክንያትም አባሪ ሆኖ ተነስቷል።

ኅብረቱ ለኤርትራ ከፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ቀሪው 120 ሚሊዮን ዶላር ጉዳይ ላይ በዚህ ሳምንት የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ እንዲሰረዝ የተጠየቀው ቀሪ የገንዘብ መጠን በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ ሌሎች ዓላማዎች እንዲውል ተጠይቋል።

በዚህ መሠረት 62 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው የሱዳንን የዴሞክራሲ ሽግግር ለመደገፍ፣ 18 ሚሊዮን ዶላር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ለተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲውል፣ ቀሪው 20 ሚሊዮን ዶላር በደቡብ ሱዳን ያለውን የምግብ አቅርቦት ችግር ለመፍታትና የተቀረው 20 ሚሊዮን ዶላር በአፍሪካ ቀንድ ለተፈናቀሉ ሰዎችና ስደተኞች ድጋፍ እንዲውል አማራጭ ሐሳብ ቀርቧል ነው የተባለው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img