Tuesday, December 3, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ከአካውንት ወጪ አድርገዋል ላላቸው ማስጠንቀቂያ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ መጋቢት 7፣ 2016 – መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ከአካውንት ወጪ አድርገዋል ላላቸው ማስጠንቀቂያ የሰጠው ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 7፣ 2016 ነው።

የባንኩ ማስጠንቀቂያ የመጣው ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ ቢያንስ ለሦስት ሰዓታት በባንኩ አካውንት ቢኖራቸውም አነስተኛ ተቀማጭ የነበራቸው ደንበኞች ካስቀመጡት ተቀማጭ በላይ መቶ ሺህ ብሮችን በሞባይል ባንኪንግ እና በኤቲኤም አስተላልፈዋል ከተባለ በኋላ ነው።

መንግሥታዊው ባንክ ስለ ጉዳዩ እስካሁን ድረስ ዝርዝር መረጃ ባያወጣም ዛሬ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ‹‹በሲስተም ችግር ምክንያት›› በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ሞባል ባንኪንግ፣ በቅረንጫፎች እንዲሁም በሲቢኢ ብር አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ አሳውቆ ነበር።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቋረጠውንን አገልግሎቱን መቀጠሉን ቢያሳውቅም አሁንም ድረስ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ማብራሪያ አልሰጠም። በአንጻሩ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ባስነገረው ማስታወቂያ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያስደረጉ ተማሪዎች በሕግ ከመጠየቃቸው በፊት “በታማኝነት” እንዲመልሱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ማስጠንቀቂያ ከተነገባቸው መካከል የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከሂሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች ዛሬውኑ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማንኛውም ቅርንጫፍ በአካል በመሄድ ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img