Thursday, November 21, 2024
spot_img

ዶክተር ሊያ ታደሰ ተሸኝተዋል

ከየካቲት 2012 አንስቶ አራት ዓመት ለተጠጋ ጊዜ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርን የመሩት ዶክተር ሊያ ታደሰ በዶክተር መቅደስ ዳባ ተተክተዋል፡፡ ተሰናባቿ ዶክተር ሊያ ታደሰ በተለይ በመጋቢት 2012 ኮቪድ19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በሰጧቸው እለታዊ መግለጫዎች ይበልጥ ይታወሳሉ፡፡

የ47 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ዶክተር ሊያ ታደሰ ቀጣይ ማረፊያቸው ያልታወቀ ሲሆን፣ አዲሷ ተሹዋሚ ዶክተር መቅደስ ዳባ ፈይሳ ዛሬ ሐሙስ ጥር 30 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የማሕፀን እና ጽንስ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው አስቀድሞ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ሠርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የጽንስ እና የማሕጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዘዳንት ሆነው የሠሩት ዶክተር መቅደስ፤ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት የማሕፀን እና ጽንስ ዲፓርትመንት ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡

በሌላ በኩል በ2021 ዓየለም አቀፍ የጽንስ እና የማህጸን ፌደሬሽን በአለም ዙሪያ በዘርፉ በምርመር አስተዋጽኦ አድርገዋል በሚል ከመረጣቸው ባለሞያዎች መሃከል አንዷ በመሆን የፊጎ ሽልማት ወስደዋል፡፡ [አምባ ዲጂታል]

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img