Thursday, November 21, 2024
spot_img

የኤርትራ ወታደሮች በድንበር አካባቢ በገበሬዎች እገታና ከብት ስርቆት ላይ ተሰማርተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ጥር 25፣ 2016 – የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ ከ15 ወራት በኋላ አሁንም ድረስ ከኢትዮጵያ መሬት ሙሉ ለሙሉ አልወጡም የሚባሉት የጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች፤ በኢትዮጵያ ድንበር በሚገኙ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ገበሬዎችን በማገት እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች ስርቆት ላይ መሰማራታቸው ተነግሯል።

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ወታደሮቹ እገታውንና ስርቆቱን የሚፈጽሙት ድንበር ላይ ባሉ ሁለት አካባቢዎች ነው።

ሆኖም የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በወታደሮቹ ላይ የቀረበውን የእገታ እና ስርቆት ውንጀላ ሐሰተኛ ነው ብለውታል።

ሚኒስትሩ ውንጀላውን ቢያስተባብሉም የዜና ምንጩ ተመለከቱት ባለው ሰነድ፣ ጥር 12፣ 2016 ወታደሮቹ 8 እረኞችን ከአህያ እና ግመሎቻቸው ጋር አፍነው ወስደዋል። ከዚህ አስቀድሞ በኅዳር ወር መገባደጃ ሁለት ቀናት ወታደሮቹ ስድስት ግለሰቦችንና 56 ከብቶችን እንዲሁም 100 እንስሳትን ሰርቀዋል።

በኢትዮጵያ እና ድንበር በርካታ አካባቢዎች አሁንም ድረስ የኤርትራ ወታደሮች ተቆጣጥረውት ስለሚገኙ ከእነዚህ አካባቢዎች በጦርነት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መመለስ እንዳልቻለ ይነገራል። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደሌሉ ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img