Tuesday, December 3, 2024
spot_img

ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በፈረመው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራሮች መካከል ክፍፍል ተፈጠረ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ጥር 22፣ 2016 – በቅርቡ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በፈረመው በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራሮች መካከል ክፍፍል መፈጠሩ ተነግሯል።

የታጣቂ ቡድኑ አመራሮች ከሳምንታት በፊቴ ከመንግሥት ጋር ከተፈራረሙ በኋላ በሰቆጣ ከተማ ይፋ ሲያደርጉ በመንግሥት መዋቅሮች ሥልጣን ታገኛላችሁ ተብለናል ሲል ተናግረው ነበር።

ከመንግሥት ጋር ስምምነቱን ከፈረሙት የታጣቂው ቡድን አመራሮች ውስጥ የቀድሞው የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ግደይ ገብረኪሮስና ሌሎች ሦስት አመራሮች መካከል ክፍፍል እንደተፈጠረ አፍሪካ ኢንተሊጀንስ ዘግቧል። አሁን በተፈጠረው ክፍፍል ግደይ ከመንግሥት ጋር የተፈረመውን ስምምነት ሲደግፉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ተቃውመውታል። ሆኖም አመራሮቹን ከስምምቱ በኋላ በተቃርኖ እንዲቆሙ ያደረጋቸው ምክንያት አልተገለፀም።

በአመራሮቹ መካከል ክፍፍል እንደተፈጠረበት የተሰማው ንቅናቄው፣ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከሕወሓት ጋር በመወገን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ተዋግቷል። ታጣቂ ቡድኑ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን ሁለት ወረዳዎች ማለትም በአበርገሌ እና በፃግብጂ አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ ይናገራል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img