Thursday, November 21, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከትግራይ ሀገረ ስብከት ጋር የነበረውን ግንኙነት ለማስቀጠል ጥሪ አቀረበች

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ የካቲት 1፣ 2015 – የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ከትግራይ ሀገረ ስብከት ጋር የነበረውን ግንኙነት ለማስቀጠል በፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ለቀ ጳጳስ ዘ አክሱም በተጻፈ ደብዳቤ ጥሪ አቅርባለች።

ዛሬ ረቡዕ የካቲት 1፣ 2015 ለአዲግራት ሀገረ ስብከት ለቀጳጳስ ለአባ መርሐ ክርስቶስ በተጻፈው የፓትሪያርኩ ደብዳቤ፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን “አላስፈላጊ” ባለችው ጦርነት በተከሰተው ችግር ያዘነች ብትሆንም በጊዜው ተፈጥሯል በተባለ የፖለቲካ ሴራ ምክንያት በትግራይ በኩል ቅሬታ እንደተፈጠረ ሠፍሯል። ቅሬታው ተገቢ መሆኑ እንደሚታመን የገለፀው ደብዳቤ፣ ምንም እንኳን ጊዜው ያለፈ ቢሆንም ከግንኙነት በኋላ በአንድነት በመወያየት አስፈላጊው ሁሉ የሚደረግ መሆኑንም ያትታል።

በመሆኑም ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት እንዲቀጥልና በአጠቃላይ አስተዳደራዊ ሥራዎች ላይ በቀጣይነት ምን መደረግ እንዳለበት በዝርዝር ለመወያየት አባ መርሐክርስቶስ አፋጣኝ በሆነ ጊዜ ግንኙነት የሚፈጠርበትን ጊዜ እንዲያመቻቹ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የትግራይ ክልል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ከእናት ቤተ ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሶ ተዋህዶ ተነጠሎ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክሕነት ለመመሥረት መወሰኑን ያሳወቀው ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ነበር።

በወቅቱ ከትግራይ ሃይማኖት አባቶች በኩል የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በተለይ ‹‹ይወክለናል ያልነው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የተደረገላቸውን ተደጋጋሚ ጥሪ ወደ ጎን በማለት የትግራይ ጀኖሳይድ ላይ ደጋፊዎች ሆነዋል›› በማለት ቅሬታ አቅርበው ነበር የራሳቸውን የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ሕህነት ለመመስረት መወሰናቸውን የገለጹት።

እነዚሁ አባቶች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጥሪ ከመቅረቡ በፊት በክልሉ መገናኛ ብዙሃን በቀረበ መግለጫ፣ “ለትግራይ ህዝብ ህልውና ደህንነት ሲባል” የተመሰረተው ቤተ ክህነት “አሁንም ለድርድር እንደማይቀርብ” ገልፀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img