Sunday, September 22, 2024
spot_img

የትግራይ ኃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት ሒደት ወራት ሊወስድ እንደሚችል የሕወሓት ቃል አቀባይ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ኅዳር 16 2015 የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት ባለፈው ጥቅምት 23፣ 2015 በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ ስምምነት የፌዴራሉን ኃይሎች የገጠሙት የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሒደት በአንድ ወር ጊዜ እንደሚፈጸም ሠፍሯል፡፡

ይኸው የጊዜ ገደብ በሚቀጥለው ሳምንት ዐርብ ጥጥምት 23፣ 2015 የሚያበቃ ቢሆንም፤ ሕወሓትን በመወከል በፕሪቶሪያ የፈረሙት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ ወራት ወራት ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ይህን የተናገሩት ከቢቢሲ ‹‹ሃርድ ቶክ›› ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡

በፌዴራል መንግሥቱ እና ሕወሓት ተወካዮች መካከል ከተደረሰው የዘላቂ ተኩስ ማቆም ስምምነት በኋላ የሁለቱም ወገኖች የጦር መሪዎች በኬንያ ተገናኝተው ይህን ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኝነታቸውን በመግለጽ ሌላ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡ በስምምነቱ የሕወሓት ትጥቅ መፍታት በኢትዮጵያ መሬት ላይ ካለው የኤርትራ ጦር መውጣት ጋር ጎን ለጎን የሚካሄድ እንደሚሆን ተገልጧል፡፡

ጌታቸው ረዳ በቆይታቸው ይኸው የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ካልወጣ ሕወሓት ትጥቅ የሚፈታበት ምክንያት የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም በፌደራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ሕወሃት ትጥቅ እንዲፈታ ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ፣ መሬት ላይ ወይም በስምምነቱ አተገባበር ላይ ‹‹ምንም የተቀየር ነገር›› እንደሌለ ጌታቸው ገልጸዋል።

በኬንያው ስምምነት ከሠፈሩ ነጥቦች መካከል ሌላኛው የመከላከያ እና የሕወሓት ወታደራዊ ከስምምነቱ በኋላ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ለወታደራዊ ኃይሎቻቸው ገለጻ ማድረግ ሲሆን፣ ማክሰኞ ኅዳር 13፣ 2015 ለትግራይ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ስለተፈረመው የሰላም ስምምነት ለታጣቂዎቻቸው የማስረዳት ሥራዎች እየተገባደዱ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ይህን ተከትሎ አሁን ከተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች መውጣት እንደሚጀምሩ አመልክተው ነበር፡፡ ስምምነቱ ይህንኑ ተከትሎ ፌደራል መንግሥቱ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች ላይ ሥልጣኑን እንዲያረጋግጥ ሰፈረበት ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ የትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ በሕወሓት ቁጥጥር ስር መሆኗን አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ እና ሕወሓት ለድፍን ሁለት ዓመት ባካሄዱተት ጦርነት በመቶ ሺዎች ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፤ ሚሊዮኖቸች ለተረጂነት የተዳረጉበት ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img