Tuesday, December 3, 2024
spot_img

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ የተካተቱበት ‹‹የአማራ ሕዝብ ተደራዳሪ ልዑክ‹‹ መቋቋሙ ተገለጸ

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ጥቅምት 12 2015 ― የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞን ያካተተ ‹‹የአማራ ሕዝብ ተደራዳሪ ልዑክ›› መቋቋሙን የአማራ ማኅበር በአሜሪካ ለዲፕሎማቶች በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ማኅበሩ ይህን የገለጸው ዐርብ ጥቅምት 11፣ 2015 ለአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፣ ለአሜሪካው ተወካይ ማይክ ሐመር እንዲሁም ለሌሎችም በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ የድርድር ልዑክ የተባለው ቡድን ከጀነራል ተፈራ ማሞ በተጨማሪ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ የአብን ተወካይ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፣ አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ እና ዶክተር ወንድወሰን አሰፋን ያካተተ ነው፡፡

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ በደብዳቤው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በሚደረገው የሰላም ንግግር ሂደት የአማራ ሕዝብን ያገለለ መሆኑ እንደሚያሳስበው ገልጧል፡፡

ማህበሩ በደብዳቤው አክሎም ለመላው ኢትዮጵያውም ሆነ ለአማራ ሕዝብ ሰላም ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር ለመሥራ ቁርጠኝነቱን የገለጸ ሲሆን፣ ሁሉም ተዋንያን አዲስ የተቋቋመውን ልዑክ በሁሉም የሰላም ድርድሮች ላይ እንዲያሳትፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል ማህበሩ ገዥው ፓርቲ ሁሉንም የአማራ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ ጋዜጠኞችን፣ አክቲቪስቶችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን እና የፋኖ ተዎጊዎችን ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም ሕወሓት በአማራ ድንበር ከሚያደርገው ጠብ ጫሪ ድርጊት እንዲቆጠብ የጠየቀው ማህበሩ፤ ሁሉም አካላት ከወልቃይት ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ፣ ጠለምት እና ራያ አስተዳደራዊ ድንበር ጋር በተገናኘ ከ1983 በፊት የነበረውን እውቅና እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img