Sunday, September 22, 2024
spot_img

ድላሚኒ ዙማ – ሌላኛዋ ሸምጋይ?

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ማይክ ሐመር ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ ሦስት የአፍሪካ አገራት የሚያደርጉትን ጉዞ ጀምረዋል፡፡ ሐመር ከኢትዮጵያ ውጪ የሚጎበኗቸው አገራት ጎረቤት ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ መሆናቸውን የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ትላንት ሰኞ መስከረም 23፣ 2015 ምሽት አስታውቋል፡፡

ሐመር ደቡብ አፍሪካ የሚያቀኑት በኢትዮጵያ ጉዳይ ደቡብ አፍሪካዊቷ ታዋቂ ፖለቲከኛ እና የቀድሞዋ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ድላሚኒ ዙማን ለማወያየት መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ የልዩ መልእክተኛው የደቡብ አፍሪካ ጉዞ እቅድ የተሰማው ባለፈው ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ ባለው ሁኔታ ላይ ዋሽንግተን ውስጥ በተደረገ ውይይት ላይ ከተሳተፉ በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ ለሰሜኑ ግጭት በአፍሪካ ኅብረት የሰላም ጥረት ውስጥ ተጨማሪ አሸማጋዮች የሚካተቱበት ሁኔታን ማንሳታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ የአሁኑ የሐመር የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ከድላሚኒ ዙማ ጋር የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ጥረትን በመደገፍ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ከአንድ ወር በኋላ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት ለመፍታት እስካሁን የተደረጉ የሽምግልና ሒደቶች ፍሬ አላፈሩም፡፡ (አምባ ዲጂታል)

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img