Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሦስት ፓርቲዎች ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ወክሎ የመደራደር ሕጋዊ ሥልጣን የለውም አሉ

አምባ ዲጂታል፤ እሑድ ሰኔ 19፣ 2014 ― ያለፉትን 19 ወራት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የቆየው ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ወክሎ የመደራደር ሕጋዊ ሥልጣን እንደሌለው ያሳወቁት ሦስት የትግራይ ፓርቲዎች ሳልሳዊ ወያነ፣ ነፃነት ትግራይ እና ባይቶና ናቸው፡፡

ፓርቲዎቹ ትላንት ለዓለም አቀፍ ኅብተሰብ በጻፉት ደብዳቤ፣ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ ብቸኛው ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብም ጠይቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሓት የትግራይን ሕዝብ እንደማይወክል ገልጸዋል፡፡

ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፣ ቢሆንም ህወሓት የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ተወካይ እንዳልሆነና እንዳይሆን ሊታወቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ፓርቲዎቹ ድርድሩን በመልካም ጎን እንቀበላለን ቢሉም ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ወካይ ሆኖ የቀረበበትን መንገድ እንደማይቀበሉት ነው ያስታወቁት።

ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሓት የትግራይን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል ብለው እንደማያምኑም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገዶች እልባት ለመስጠት ባለመቻሉ ምክንያት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ጦርነት መግጠሙ የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img