አምባ ዲጂታል፤ ሰኞ ሰኔ 06፣ 2014 ― ኢትዮጵያ በ2010 ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ እና ከሶማሌላንዱ ጋር የተጋራችውን የበርበራን ወደብ 19 በመቶ ድርሻ አጥታዋለች የሚባልበት ደረጃ ላይ እንዳልደረሰች የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ገልጸዋል፡፡
ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የወደቡን ባለቤትነት በተመለከተ ንግግሮች አሁንም እንደቀጠሉ እና ተጨማሪ ሥራዎች የሚቀሩ እንዳሉ ገልፀው፤ ኢትዮጵያ ባለቤትነቷን አጥታለች የሚባልበት ደረጃ አልደረሰም፡፡
የኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ ድርሻ ማጣት ዜና የመጣው የሶማሊላንድ የገንዘብ ሚኒስትር የአገሪቱ መንግስት የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ኢትዮጵያ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ የ19 በመቶ ድርሻዋን አጥታለች ብለው ነበር።
በ2010 በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በተፈረመው የበርበራ ወደብ ሥምምነት መሠረት ኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ ስትወስድ፣ ዲ ፒ ወርልድ የተባለው ዓለም አቀፍ የወደቦች አስተዳዳሪ ኩባንያ 51 በመቶ እና የሶማሌላንድ መንግሥት ደግሞ ቀሪውን 30 በመቶ ድርሻ ወስደዋል፡፡