Thursday, November 21, 2024
spot_img

የአሜሪካ ኮንግረስ በትግራይ ጦርነት የውጭ አገራት ተሳትፎ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ

(አምባ ዲጂታል) ቅዳሜ የካቲት 5፣ 2014 ― የአሜሪካ ኮንግረስ አስራ አምስት ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ጦርነት የውጭ አገራት የነበራቸው ተሳትፎ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉ ታውቋል፡፡

አዲስ የቀረበው የውሳኔ በጦርነቱ ውስጥ የውጭ አገራት በጦር መሣሪያ ሽያጭ እና ሁኔታዎችን ማመቻቸታቸው ምርመራ እንዲደረግ የሚጠይቅ ነው፡፡

በቀጣይ ጊዜያት ድምጽ የሚሠጥበት የውሳኔ ሐሳብ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በጦርነቱ የቻይና፣ ኢራን፣ ሩስያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች፣ ሱዳን፣ ግብጽ እና ቱርክ የነበራቸውን የድርጊት ተሳትፎ እንዲገልጽ ኃላፊነት የሚሰጥ ነው፡፡

ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 1 ለኮንግረሱ ያለፈው የውሳኔ ሐሳብ፣ መቼ ድምጽ እንደሚሰጥበት ያልተገለጸ ቢሆንም፣ ኮንግረሱ ውሳኔውን ደግፎ ድምጽ የሚሰጥ ከሆነ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈርመውበት ወደ ትግበራ የሚገባበት ነው፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተለያዩ ማዕቀቦችን እንዲጥሉ የሚጠይቀው የውሳኔ ሐሳብ፣ ከእቀባዎቹ መካከል የንብረት እገዳ፣ የቪዛ ክልከላ እና የጦር መሳሪያ ማስመጣትን መከልከል የሚል አካቷል፡፡

በተጨማሪም የውሳኔ ሐሳቡ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከሰብአዊ ድጋፍ ውጭ፣ የብድር ማራዘሚያም ሆነ ቴክኒካዊ ድጋፍ እንዳይሰጡ የሚጠይቅ አንቀጽ አለው፡፡

የውሳኔ ሐሳቡ አክሎም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፣ ኔቶ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የአፍሪካ ኅብረት ማዕቀብ እንዲጥሉ ይጠይቃል፡፡  

የውሳኔ ሐሳቡ ለኮንግረስ መቅረቡን ተከትሎ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጫና በመቃወም የሚታወቀው የአሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቲ የውሳኔ ሐሳቡን በመቃወም ሰልፍ ጠርቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ድረስ ስለ ውሳኔ ሐሳቤ ያለው ነገር ባይኖርም፣ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው የውሳኔ ሐሳቡ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው ብለውታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img