አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥር 28፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ እንዲገኙ ጥሪ እንዲተላለፍላቸው መወሰኑ ተሰምቷል፡፡
በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር የሚወያው ሲኖዶሱ፣ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በመንበረ ፓትሪያርኩ እንዲገኙ ያለው የካቲት 4፣ 2014 ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬተርያት ባለፈው ረቡእ ይፋ ባደረገው መረጃ፣ በእለቱ በከተማ አስተዳደሩ ኃላፊዎች እና በሲኖዶሱ መካከል ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በላከው መልእክት በስብሰባው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝ በመጠየቅ›› ስብሰባው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሆኖም ቅዱስ ሲኖዶሱ የከተማ አስተዳደሩ ስላወጣው መረጃ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡