Sunday, September 22, 2024
spot_img

ጠ/ሚ ዐቢይ መንግሥታቸው ከሕወሓት ጋር ድርድር እንደሚያደርግ መናገራቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥር 18፣ 2014 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥታቸው ከሕወሓት ጋር ድርድር እንደሚያደርግ መናገራቸውን የዘገበው አሶሺየትድ ፕረስ ነው፡፡

የዜና ወኪሉ ይህንኑ ለአምስት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት አድርገናል ያሉት የአሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌይርስ ኮሚቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ መስፍን ተገኑ እንደነገሩት ነው የዘገበው፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ጦርነቱን ለማቆም ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹በርግጥ ይህ እንዲሆን ሌላኛው ወገንም ፍቃደኛ መሆን አለበት›› ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡ አክለውም ‹‹የአገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይኖራል›› ስለማለታቸውም አሶሽትድ ፕረስ አቶ መስፍን ተገኑን ጠቅሶ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ሊቀመንበሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስት የትግራይ ሕዝብ የሕወሓት ሰዎችን ወደ ድርድር እንዲገፋቸው ይፈልጋል እንዳሉም ነው የተመላከተው፡፡   

ሊቀመንበሩ አያይዘውም ኢትዮጵያን ከሰሞኑ የጎበኙት አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀን ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ስለዚሁ ሂደት ሳያውቁ እንደማይቀሩ ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ደርሰው ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ ያቀኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ፣ የኢትዮጵያ ቆይታቸውን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ የለም፡፡

አሶሽየትድ ፕረስ ስላወጣው ዘገባ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽሕፈት ቤትም ሆነ ከሕወሓት ኃይሎች በኩል ምላሽ አልተሰጠበትም፡፡

በፌዴራል መንግስት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት 15 ወራት አስቆጥሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img