Saturday, October 12, 2024
spot_img

ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቅ ‹ይበቃል› የተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው

  •  

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥር 16 2014 ― በሳዑዲ ዐረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት የጀመረውና ‹ይበቃል› በሚል መሪ ቃል በሳዑዲ እስር ቤቶች የሚገኙ በርካታ ሺሕ ኢትዮጵያውያን ለብሰው የሚተኙበትን ጥቁር ፌስታል በማድረግ የሚካሄደውን ዘመቻ በርካቶች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ 80 ሺሕ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዐረቢያ እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ባለፉት ቀናት እየተካሄደ የሚገኘው ዘመቻም፣ የሳዑዲ ዐረቢያ መንግስት ለነዚህ እስረኞች መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽም እንዲሰጥ እና ጉዳዩ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጠው ለመጠየቅ አላማ ያለው ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሳዑዲ ዐረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያንን ለመመለስ የሚሠራ ልዑክ ወደ አገሪቱ ሊያቀና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የገለጹ ቢሆንም፣ እስካሁን ልኡኩ ወደ አገሪቱ ስለማቅናቱ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ የሚያቀናው የልዑካን ቡድኑ ከሃማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ እንደሚሆን ተጠቁሞ ነበር፡፡

በአገሪቱ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት ችግራቸውን ተመልክቶ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img