Sunday, November 24, 2024
spot_img

አዲሱ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥር 14፣ 2014 ― ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አዲሱ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ፣ በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ መሕመት ፈቂ ጋር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሳተርፊልድ አዲስ አበባ የመጡት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ ጋር ሲሆን፣ ሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ባለፉት ቀናት በሌሎች አገራት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ሳተርፊልድ እና ሞሊ ፊ ጉብኝት ካደረጉባቸው አገራት መካከል ቀድሞ ሳዑዲ ዐረቢያ ሲገኙ፣ ከዚያም የፖለቲካ መረጋጋት በራቃት ሱዳን ቆይታ አድርገዋል፡፡ በሱዳን ቆይታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

አሁን አዲስ አበባ የሚገኙት አዲሱ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ፣ በቆይታቸው ከየትኞቹ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ዴቪድ ሳተርፊልድ ለዘጠኝ ወራት የአሜሪካ ልዩ መልእከተኛ ሆነው ያገለገሉትን አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን የተኩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img