Sunday, November 24, 2024
spot_img

አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥር 7፣ 2014 ― ያለፉትን ዘጠኝ ወራት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን የተኩት ዴቪድ ሳተርፊልድ፣ በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብሏል።

ሳተርፊልድ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ እና ሱዳን በሚያደርጉት ጉብኝት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ረዳት ሚኒስትሩ ሞሊ ፊን እንደሚያስከትሉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል።

በቅድሚያ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ የሚጠበቁት ልዩ መልዕክተኛው፣ ቀጥሎ ካርቱምንና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ነው የተባለው።

ሳተርፊልድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ መረጋጋት ወደራቃት ሱዳን ተጉዘው ከተለያዩ የለውጥና የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር እንዲሁም ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር እንደሚወያዩም ተነግሯል፡፡

ሳተርፊልድ የተኳቸው አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን፣ ከቀናት በፊት በመንግስት ግብዣ አዲስ አበባ ተገኝተው እንደነበር ይታወቃል። ፌልትማን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ተከትሎም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ስልክ ደውለው መወያየታቸው መነገሩ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img