Thursday, October 17, 2024
spot_img

የመንግስታቱ ድርጅት በማይ ዐይኒ የስደተኞች መጠለያ በተሰነዘረ የአየር ጥቃት ሦስት ኤርትራዊያን ስደተኞች ተገድለዋል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 29 2014 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትግራይ ክልል በሚገኘው ማይ ዐይኒ የስደተኞች መጠለያ በተሰነዘረ የአየር ጥቃት ሦስት ኤርትራዊያን ስደተኞች ተገድለዋል ሲል አሳውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ሕፃናት እንደሆኑ መግለጻቸውን የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከሞቱት በተጨማሪ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ያስታወቁት ግራንዲ፣ ነገር ግን ጉዳታቸው ለሕይወታው አስጊ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ዝርዝር ሁኔውን መሰብሰብ እና ማረጋገጡን ይቀጥላል ያሉት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ፣ በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ስደተኞችን ጨምሮ የሲቪል ዜጎችን መብት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት በአየር ጥቃት ተገድለዋል ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞን በተመለከተ ከመንግስትም ሆነ ከሌላ ወገን የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img