Thursday, November 21, 2024
spot_img

የሕወሓት ሊቀመንበሩ የትግራይ ክልል ቀጣይ ዕጣ የሚወሰነው በሕዝቡ ፍላጎት ነው አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ታኅሣሥ 28 2014 የሕወሓት ሊቀመንበሩ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ቀጣይ ዕጣ የሚወሰነው በሕዝቡ ፍላጎት ነው ያሉት ከሲኤኤን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ነው፡፡

ሊቀመንበሩ ይህን የተናገሩት በቴሌቪዥን ጣቢያው ትግራይ ከተቀረው ኢትዮጵያ ራስዋን የመነጠል እድል አላት ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ደብረጺዮን በምላሻቸው እሱን መገመት አልችልም፤ ሂደቱ የሚወስነው ነው፤ መነጠልም ሆነ በፌዴራል መንግስቱ ስር መቀጠል ሊኖር ይችላል፤ ብዙ አማራጮች አሉ እኔ ወይም ፓርቲዬ ሳንሆን ሕዝብ የሚወስነው ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የሕወሓት ሊቀመንበሩ በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ሰዎች በምግብ እና መድኃኒት እጥረተ እየሞቱ ነው፤ ትግራይ በከበባ ስር ትገኛለች ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ይህን ቢሉም በትላንትናው እለት መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ፣ በአሁኑ ወቅት የትግራይ ህዝብ በርካታ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዉስጥ እንደሉበት መንግስት መገንዘብ ብቻ ሳይሆን የሕዝባችን አንዱ አካል በመሆኑ እነዚህ ችግሮቹ እንዲፈቱለት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

እነዚህ ጥቅሞቹ እና መብቶቹ እንዲከበሩ ከተፈለገ ‹‹በጦርነት ብቻ የመኖር ፍላጎትና ጥማት›› አለበት ያሉት ሕወሓት ‹‹ዳግም የትግራይን ህፃናት በጦርነት እንዳይማግድ የጦርነትና የግጭት አባዜውን ማስቆም ይኖርበታል›› ብለዋል፡፡

አያይዘውም በትግራይ ክልል፣ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችና በውጭ ያለዉ የትግራይ ማህበረሰብም የትግራይ ክልልና ህዝብ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ እንዲመለስ፣ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዲፈቱና ዘላቂ ጥቅሞቹ እንዲረጋገጡ የበኩለቸዉን ድርሻ መወጣት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡  

በሌላ በኩል ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በሲኤንኤን ቆይታቸው የሕወሓት ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ ተጠግተው በነበረበት ወቅት አሜሪካን ጨምሮ ወደ ከተማዋ እንዳንገፋ ሲጠይቁን ነበር ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር መገባደጃ በትግራይ ተጀምሮ በዓመቱ መጨረሻ ወራት የፌዴራል መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም በማዋጅ ትግራይን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የሕወሓት ኃይሎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ገፍተው በርካታ አካባቢዎችን ተቆጣጥረው ቆይተዋል፡፡

ሆኖም በኅዳር ወር አጋማሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መከላከያን ለመምራት ወደ ግንባር አቅንቻለሁ ካሉበት ጊዜ አንስቶ የፌዴራል መንግስት ኃይሎች የአማራ እና አፋር አካባቢዎችን ዳግም ተቆጣጥረዋል፡፡

አስራ አራት ወራት ያስቆጠረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት በቅርብ ቀናት ጋብ ማለቱ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img