Saturday, October 12, 2024
spot_img

በሳዑዲ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 26፣ 2014 ― በሳዑዲ ዐረቢያ እስር ቤት የሚገኙ በርካታ ሺሕ ኢትዮጵያውያን ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

አል ዐይን አማርኛ በድረ ገጹ ባጋራው ዜና በአገሩ እስር ቤት ከሚገኙ ኢትዮጵያውን መካከል በእስር ቤት ውስጥ ሕፃናት በርሃብ እና በበሽታ ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል የሆነች ሴት ‹‹በአንድ ከፍል ውስጥ እስከ 500 ሰዎች ባንድ ላይ ታስረናል፣ ምግብ በቀን አንዴ ጊዜ ብቻ ይሰጠናል እሱም በቂ አይደለም፤ የልጄ ጤናም በየቀኑ እየተባባሰ ነው እንዳላጣት ፈርቻለሁ›› ብላለች፡፡

በሳዑዲ ሺመሺ እስር ቤት ከታሰረች አንድ ዓመት ሊሞላት መሆኑን የገለጸች ሌላ ታሳሪም፣ ከታሰረችበት ጊዜ ጀምሮ የሳዑዲ ፖሊስ የሰጣትን አንድ ልብስ ብቻ እንደለበሰች ተናግራለች፡፡

ታሳሪዋ ‹‹በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እየረዳን አይደለም፡፡ በየቀኑ ልጆቹ እየሞቱ ነው፡፡ በር የሚከፈትልን ሰው ሲሞት ብቻ ነው፡፡ ፖሊሶች ሰው ታሟል ብላችሁ በር እንዳታንኳኩ ብለውናል›› ስትል ሁኔታውን ተናግራለች፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር በእስር ላይ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው ሲመለሱ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

አሁንም ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው የመመለሱ ሂደት አለመቆሙን ጠቁመው የተወሰነ መቀዛቀዝ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ይሁንና እንደከዚህ በፊቱ በአስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ 80 ሺሕ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዐረቢያ እስር ቤቶች እንደሚገኙ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img