Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሕዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ቀናት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 25 2014 ኢትዮጵያ በዐባይ ላይ የምትገነባው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ዝግጅት እንደተጠናቀቀ ተነግሯል፡፡

የሕዳሴው ግድብ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ዝግጅት ተጠናቋል መባሉን ምንጮቼ ነግረውኛል ያለው ካፒታል ጋዜጣ ነው፡፡

ግንባታው ከተጀመረ አስር ዓመት የሞላው የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ሙሌቱ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ ግድቡ በአሁኑ ወቅት 82 በመቶ ተጠናቋል ነው የተባለው፡፡

ይህንኑ ተከትሎ ግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨቱን ሲጀምር 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ ተነግሮለታል፡፡

ግዙፉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሱዳንና ግብፅ ጋር ሲያነታርካት ቆይቷል፡፡ በግድቡ ላይ የሚካሄደው ድርድር መቋጫ ያላገኘ ቢሆንም፣ ከቀናት በኋላ ኃይል ወደ ማመንጨቱ ተቃርቧል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የኃይል ማመንጫ ግድቦቿ 4 ሺሕ 967 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጭ ሲሆን፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ የኃይል ማመንጨት አቅሟን በእጥፍ ያሳድገዋል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img