Thursday, July 4, 2024
spot_img

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ጊቢውን መልቀቅ ላልቻሉ ተማሪዎቹ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 23፣ 2014 ― አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ዓመት ተመርቀው ጊቢውን መልቀቅ ላልቻሉ ተማሪዎቹ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲውን ያልለቀቁት እነዚህ 41 ተማሪዎች ግጭት ከተከሰተባቸው ትግራይ፣ ወለጋ እና መተከል አካባቢ ሲሆኑ፣ ዩኒቨርሲቲው እስከተያዘው ወር መጨረሻ ለቃችሁ ውጡ ማለቱን ሪፖርተር አስነብቧል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ማቴዎስ ኤርሳሞ እንደገለጹት፣ ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት የሚያበቃው እስከ ምርቃት ቀናቸው ቢሆንም፣ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ በማስገባት እስካሁን እንዲቆዩ አድርጓል።

ሆኖም ዩኒቨርሲቲው ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት እንዲቆዩ ቢያደርግም፣ አንዳንዶቹ ከተማ ውስጥ ሥራ አግኝተውም ቢሆን እዚያው መቆየትን መርጠዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ከሆነ ሌሎቹ ደግሞ በመጡበት አካባቢ ግጭት እንዳለ ቢናገሩም፣ ትክክለኛ አካባቢው የት እንደሆነ ሊናገሩ ስላልቻሉ ምክንያታቸው ትክክለኛ ይሁን አይሁን ማረጋገጥ አልቻሉም።

ከተመራቂዎቹ መካከል ከትግራይ ክልል የመጡ እንደነበሩ ያስታወሱት ዶክተር ማቴዎስ፣ ከመካከላቸው በርካቶቹ ሥራ በማግኘትም ይሁን ወደ አካባቢያቸው በመመለስ ጊቢውን ስለለቀቁ አሁን በዩኒቨርሲቲው የሚገኙት ጥቂት ናቸው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባለፈው ዓመት ተማሪዎቹን ያስመረቀው በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img