Sunday, October 6, 2024
spot_img

በደቡብ ሱዳን ዳግም ግጭት ሊያገረሽ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስጋቱን ገለጸ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_text_color=”#242E3F” text_font_size=”18px” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን ዳግም ግጭት ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ባወጣው ሪፖርት አሳውቋል፡፡

የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች የደረሱት የሰላም ስምምነት አፈጻጸም መጓተት አገሪቱን ዳግም ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያስገባ እንደሚችል ድርጅቱ ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ 3 ዓመት ሞልቷል ያለው የመንግሥታቱ ድርጅት፣ ሆኖም ግን በፕሬዚዳንት ሳለቫ ኪር እና በተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል አልፎ አልፎ ግጭቶች እንደሚስተዋሉም ገልጿል።

ደጋፊዎች መካከል የሚስተዋሉት ግጭቶች ለደቡብ ሱዳን ዜጎች አስፈላጊ የሆኑ የሰብአዊ ድጋፎች እንዳደርሱ እያደረገ መሆኑን በመግለጽ፣ ይህም የሀገሪቱን ዜጎች ለከፋ ጉዳት እየዳረገ መሆኑን አስታውቋል።

አዲሱ የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት አክሎም የሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዳይሆን እንቅፋት በሚሆኑ የሀገሪቱ የፖለቲካ ሀይሎች ላይ የአዲስ የጦር መሳሪያ ግዢ ማእቀብ እንዲጣል እና ከዚህ በፊት የተጣሉ ማእቀቦችም እንዲራዘሙ ጠይቋል።

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img