Sunday, October 6, 2024
spot_img

ንብረትነቱ የሕወሃት የሆነ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ማድረጉን ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_text_color=”#242E3F” text_font_size=”18px” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃበየ ሕግ ንበረትነቱ ሕወሃት ‹‹ለወንጀል ድርጊት መፈጸሚያነት ሊያውለው ነበር›› ያለውን 6 ነጥብ 7 በሊዮን ብር እንዳይንቀሳቀስና በሕገ ወጥ መንገድ እንዳያሸሽ መከላከል መቻሉን አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕወሃት በጥቅምት ወር በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወነዉ የሐብት ክትትልና ምርመራ ሥራ ቡድኑ ‹‹ለሕገ ወጥ አላማ ሊጠቀምበት›› ነበር ያለውን ገንዘብ በሕግ አግባብ የውርስ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሚመለከተዉ አካል መተላለፉንም ነው የገለጸው፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ሐብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል የሆኑት አቶ ዓለምአንተ አግደው ጨምረው እንዳሉት ‹‹ኢትዮጵያን ከድተው ከሕወሃት ጋር በመሰለፍ በጦርነት የተሳተፉ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች ገንዘብና ሃብት ላይ በተደረገ ክትትልና ማጣራት ሥራ አምሳ አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺሕ አምስት መቶ ስልሳ አምስት ብር እንዲሁም ሌሎች ብዛት ያላቸዉ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ ተደርጓል››፡፡

በኤፈርት ሥር በሚተዳደሩ እና ተያያዥ የሆኑ የተለያዩ ድርጅቶች ላይ በተከናወነ የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ አራት ቢሊዮን ሁለት መቶ አምስት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ሰባት ሺሕ ስልሳ አንድ ብር በፍ/ቤት ትዕዛዝ በማሳገድ እና ግምታቸዉ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ 179 የደረቅና የፈሳሽ ጭት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለማሸሽ ጥረት ሲያደርጉ የፍ/ቤት ትዕዛዝ በማውጣትና የጋራ የሕግ ትብብር ጥያቄ ለጅቡቲ መንግስት በማቅረብ ወደ አገር ማስመለስ መቻሉንም ተገልጧል፡፡

በተመሳሳይ በሕወሃት በስሩ በነበሩ አመራሮች ቀጥተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸዉ በነበሩና ዐቃቤ ሕግ ቡድኑ የድርጅቶችን ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያ ሊያውል ይችሉ ነበሩ ያላቸውን ሦስት ሲቪል ማህበራት ላይ በተደረገው በተደረገ የሐብት ክትትልና ምርመራ ሥራ አራት መቶ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ አምስት ሺሕ አምስት መቶ ሃያ ሰባት ብር በፍ/ቤት ትዕዛዝ በማሳገድ እና ገለልተኛ አስተዳዳሪ በፍ/ቤት በማሾም የማህበራቱ ገንዘብ በሕወሃት ዓላማ እንዳይውል መከላከል ተችሏልም ተብሏል፡፡

በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄነራሉ፣ በተከናወነው የሐብት ክትትልና ምርመራ ሥራ ደግሞ የሕወሃት የሆነ ብር ዘጠና ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺሕ አንድ መቶ ስልሳ አራት ብር የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፍ/ቤት ትዕዛዝ በማሳገድ ለወንጀል ተግባር እንዳይውል መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img