Sunday, November 24, 2024
spot_img

የነዳጅ ድጎማን ከተመረጡ ተሸከርካሪዎች በሒደት የሚቀንስ እና የሚያስቀር የውሳኔ ሐሳብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 20፣ 2014 ― መንግሥት የሚያደርገውን የነዳጅ ድጎማን ከተመረጡ ተሸከርካሪዎች በሂደት የሚቀንስ እና የሚያስቀር የውሳኔ ሐሳብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡

ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባው የነዳጅ ድጎማን ከተመረጡ ተሸከርካሪዎች በሂደት ለመቀነስና ለማስቀረት የሚያስችል የዋጋ ማስተካከያ ጥናት በማድረግ የቀረቡ የውሳኔ ሀሳቦችን ለመተግበር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘጋጅቶ ተዘጋጅቶ ተመልክቶታል፡፡

በቀረበው አጀንዳ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ፣ የውሳኔ ሐሳቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ከዛሬ ጀምሮ ከስድስት ወር የዝግጅት ምዕራፍ በኋላ ተፈፃሚ እንዲሆን ወስኗል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ ነዳጅ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወትና ከህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የተቆራኘ የሀይል ምንጭ በመሆኑ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋው በኢኮኖሚው እና በህብረተሰቡ ላይ የጎላ ተጽእኖ እንዳይፈጥር በመንግስት እየተወሰነና ቁጥጥር እየተደረገበት ሲሰራበት መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ሆኖም የሀገሪቱን ወቅታዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎችንና የህብረተሰቡን የኑሮ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀገር ውስጥ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የዓለም አቀፉን ዋጋ በሚያንጸባርቅ መልኩ እየታየና በየጊዜው እየተከለሰ ወደ ሸማቹ እንዲተላለፉ ባለመደረጉ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ እዳ በዋጋ ማረጋጊያ ፈንዱ ላይ እየተከማቸ እንደሚገኝ ገልጧል፡፡

የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ በአሁኑ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል ለተባለው በፖሊሲ ያልተደገፈ የነዳጅ ድጎማ ለማስተካከል ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img