Sunday, October 6, 2024
spot_img

በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ሰበብ በሰው እርዳታ የሚንቀሳቀሱ ከብቶች ቁጥር ከመቶ ሺሕ በላይ መድረሱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 19 2014 በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሰበብ በሰው እርዳታ የሚንቀሳቀሱ ከብቶች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡

አሐዱ ራዲዮ የኦሮሚያ ክልል መስኖ እና ልማት ቢሮን ጠቅሶ እንደዘገበው በክልሉ በቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሐረርጌ እንዲሁም ምሥራቅ ባሌ በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ እስካሁን ከ72 ሺሕ በላይ ከብቶች ሞተዋል፡፡

የክልል የመስኖ እና ልማት ቢሮ የጥናትና ምርምር ቢሮ ዳይሬክተር ከተማ ኡርጎ በድርቁ ሳቢያ በሰው ሀይል የሚንቀሳቀሱ ከብቶች ቁጥር አንድ መቶ 19 ሺሕ 935 መድረሱን ለራድዮው ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በመንግስትም በሚመለከታቸው አካላትም የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ የድርቁ ስፋት ከፍተኛ በመሆኑ አሁንም ርብርቡ መቀጠል እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

ድርቁ በከፍተኛ መጠን ጉዳት እያደረሰ መሆኑ በተነገረበት በተለይም በቦረና፣ በአካባቢው የሚገኙት ነዋሪዎች አርብቶ አደር በመሆናቸው የጉዳት መጠኑን ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ከችግሩ ስፋት አንፃር አሁንም የበርካቶችን ርብርብ የሚጠይቅ ነው ያሉ ሲሆን ድርቁ እስከ 3 ወር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺሕ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ከፍ እንዳለም ተገልጿል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img