Friday, November 29, 2024
spot_img

ለመልሶ ማቋቋም የ5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 18፣ 2014 ― በጦርነትና በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የአምስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መዘጋጀቱን የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ገልጸዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የሚመራው የመልሶ ማቋቋም ሴክሬታሪያት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዐርብ ታኅሣሥ 15፣ 2014 በገንዘብ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ የመጀመሪያውን ውይይት አድርጓል።

በዚሁ ውይይት ወቅት ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እንደገለጹት በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የአምስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን በመጠቆም ተጨማሪውን በጀት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳጸደቀው በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

መንግስት ከሚመድበው መነሻ በጀት በተጨማሪም ከልማት አጋሮች በተለይም ከዓለም ባንክ ለመልሶ ማቋቋሙ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚጠበቅ የገለጹት አቶ አሕመድ፣ የመልሶ ማቋቋሙ መርሀ ግብሩ በመንግስት የሚመራ፣ የተቀናጀ፣ በየደረጃው በፕሮግራም ተግባራዊ የሚደረግ፣ ተጠያቂነት ያለውና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚተጋ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በጦርነቱና በግጭቱ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅና በገንዘብ ለመተመን የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል የመነሻ ሀሳብ በገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለመልሶ ማቋቋም ሴክሬታሪያት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የቀረበ ሲሆን፣ የኮሚቴ አባላትም የመልሶ ማቋቋም መርሀ ግብሩ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍሎች በተጨማሪ በሌሎች ክልሎች በግጭት የተፈናቀሉትንም እንዲያካትት፣ የሀብት አሰባሰብ ድግግሞሽ እንዲወገድና በአንድ ቋት እንዲሰባሰብ፣ ክልሎች ንቁ ተሳትፎ የሚደርጉቡት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች፣ ከሌሎች መሰል ብሄራዊ ኮሚቴዎች ጋር በቅንጅት እንዲሰራና የግሉን ዘርፍና ዲያስፖራውን እንዲያሳትፍ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img