Friday, November 22, 2024
spot_img

ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 16 2014 ― ታዋቂው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ በ53 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል፡፡

ቢቢሲ ቤተሰቦቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ተስፋዬ ገብረአብ ለወራት በህመም ላይ ቆይቶ ኬንያ ዋና ከተማ ውስጥ ህክምና በመከታተል ላይ እያለ ትላንት ዐርብ ከሰዓት በኋላ ታኅሣሥ 15፣ 2014 ነው ያረፈው።

በፖለቲካ ቀመስ በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቹ በስፋት የሚታወቀው ተስፋዬ ነሐሴ 22፣ 1960 ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 40 ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ በምትገኘው በቢሾፍቱ ከተማ ነበር ተወልዶ ያደገው።

ቤተሰቦቹ መነሻቸው ኤርትራ ሲሆን፣ ከኤርትራ ድባርዋ ወደ መሐል አገር በመምጣት ኑሯቸውን ቢሾፍቱ ላይ አደላድለው ለዓመታት በመኖር ልጆችን አፍርተዋል።

ተስፋዬ ገብረአብ በተለይ ሰከገዢው ኢህአዴግ ፓርቲ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበረው “እፎይታ” መጽሔትን በመምራትም ይታወሳል።

ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የእፎይታ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅትም እሱ በወጣትነት ጊዜው የገጠመው የአሳታሚ እጦት ችግር ለመቅረፍ በሚል፣ የበርካታ ወጣት ደራሲያን ሥራዎችን በማሰባሰብ በተከታታይ ቅጾች ሥራዎቻቸው እንዲታተም እድል ከፍቷል።

በዚህም ተስፋዬ ‘እፍታ’ በሚል ርዕስ በሁለት ተከታታይ ዓመታት አምስት ቅጾችን በማሳተም ለንባብ አብቅቶ ነበር።

ተስፋዬ በኢትዮጵያ ሳለ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎን መጽሐፍቶችንም ያሳተመ ሲሆን፣ የጋዜጠኛው ማስታወሻ፣ የደራሲው ማስታወሻ እና አወዛጋቢ የነበረው የቡርቃ ዝምታ የተሰኘው ረዥም ልቦለዱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img