አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሀገረ ማሪያም ከሰም ወረዳ ሾላ ገበያ የሕዝብ መናኸሪያ ትላንት ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ 4 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት አስታውቋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ደምሰው ዳኜ እንደገለጹት አደጋው ሌሊት 5 ከ 30 አካባቢ በአንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ የተፈጠረ እሳት ወደሌሎችም ተዛምቶ በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑነን የገለፁት ኮማደሩ፣ በሚኒባስ ተሽከርካሪው የሞተር ክፍል የኤሌክትሪክ መስመር መገናኘት ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡
በአደጋው የእሳቱ መነሻ ተሽከርካሪ ሙሉ ለሙሉ ሲወድም፣ ከጎኑ የነበረ በተለምዶ ዶልፊን የሚባል ተሽከርካሪ በከፍተኛ ሁኔታ መቃጠሉንም ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው በሌላ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ አይሱዙና ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን ጠቅሰው፣ በፖሊስ አባላት እና በማኅበረሰቡ ትብብር የጉዳት መጠኑን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል።
የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤትም የመናኸሪያውን የእለቱን ጥበቃ በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም የዘገበው ፋና ነው።
[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]