Friday, November 29, 2024
spot_img

የአማራ ክልል በጦርነት ለደረሰበት ኪሳራ ከፌዴራል መንግሥት ማካካሻ ሊጠይቅ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 16፣ 2014 ― በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት ወደ አጎራባች ክልሎች ሲዛመት በሕወሓት ኃይሎች ውድመት ያስተናገደው የአማራ ክልል በጦርነት ለደረሰበት ኪሳራ ከፌዴራል መንግሥት ማካካሻ ሊጠይቅ መሆኑ ተነግሯል።

የክልሉን የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህን የጠቀሰው ሪፖርተር ጋዜጣ፣ የአማራ ክልል በተለያዩ ዘርፎች ለደረሰው ውድመት ማካካሻውን ለመጠየቅ በጥናት ላይ ይገኛል።

ክልሉ ከዚህ ቀደም በጤና ዘርፍ ለገጠመው ውድመት ብቻ ሁለት ቢሊዮን ብር ጠይቋል።

የአማራ ክልል የሕወሓት ኃይሎች ይዘዋቸው በነበሩ አካባቢዎች በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ቡድን ማሰማራቱም ነው የተነገረው።

ጥናቱን የሚያስተባብረው የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሲሆን፣ ከክልሉ መሥሪያ ቤቶች ብቻ 120 የሚጠጉ ባለሞያዎች የተሳተፉበትና የተለያዩ የሙያ ስብጥሮች ያሉት ቡድን በክልሉ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት ለማጥናት ተሰማርቷል።

ከጥናቱ በኋላ ግምቱ ይፋ እንደሚደረግ የገለጹት የኮሚኒኬሽን ኃላፊው፣ በርካታ ቢሊዮን ብር ሊሆን እንደሚችል ነው ያመለከቱት።

የአማራ ክልል መንግስት በጥቅምት ወር መገባደጃ የሕወሓት ኃይሎች ድንበር ተሻግረው የተለያዩ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ በስሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን አቋርጠው በጀትን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ለጦርነት እንዲያውሉ ወስኖ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img