Friday, November 29, 2024
spot_img

ፖሊስ መዐዛ መሐመድን ከሕወሓት ተልእኮ በመቀበል ወንጀል ጠርጥሮ እየመረመራት እንደሚገኝ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 16፣ 2014 ― የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋለችው የሮሃ ቲቪ መስራች መዐዛ መሐመድን ከሕወሓት ተልእኮ በመቀበል ወንጀል ጠርጥሮ እየመረመራት እንደሚገኝ አሳወቀ።

ፖሊስ በኮማንድ ፖስቱ ስር ስለምትገኝም ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደማይችል ገልጿል።

ፖሊስ ይህን ያለው መዐዛ መሐመድ ታኅሣሥ 14፣ 2014 ለፍርድ ቤት በጻፈችው አቤቱታ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያለ አግባብ አስሮኛል ማለቷን ተከትሎ በሰጠው ምላሽ ነው፡፡

ፖሊስ ለፍርድ ቤት በሰጠው ምላሽ መዐዛ መሐመድ ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋለችም አብራርቷል፡፡

ፖሊስ በደብዳቤው ለመዐዛ እስር ምክንያት የሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ሕወሓትን በመደገፍ እና ተልእኮ በመቀበል የተለያዩ ሐሰተኛ ያላቸው ‹‹ሕዝብን እና መንግስትን የሚለያይ፣ የኅብረተሰብ ጤናማ እንቅስቃሴ የሚያውክ እንዲሁም በመንግስት ላይ ጥርጣሬ የሚፈጥር መረጃዎችን እና በርካታ ሕዝቡን ለሁከትና ብጥብጥ የሚያነሳሱ መልእክቶችን›› በማስተላለፏ ነው ብሏል፡፡

መዐዛ መሐመድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በሚገኘው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስራ እንደምትገኝ ከዚህ ቀደም ቤተሰቦቿ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፡፡

መዐዛ መሐመድ በቁጥጥር ስር ከመዋሏ በፊት ትሠራበት ከነበረው ሮሃ ቲቪ የተሰኘ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን በፊት፣ ዐባይ በተባለ መገናኛ ብዙኃን በምታቀርባቸው ዝግጅቶች በሥፋት ትታወቃለች፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img