አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 16፣ 2014 ― በትግራይ ክልል ከፊታችን ሰኞ ታኅሣሥ 18፣ 2014 ጀምሮ እስከ ረቡዕ ታኅሣሥ 20፣ 2014 ድረስ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ጾም እና ጸሎት መርሐ ግብር ታውጇል፡፡
የክልሉ ብዙኃን መገናኛዎች እንደዘገቡት የጾም እና ጸሎት መርሐ ግብሩ የታወጀው በክልሉ እየተፈመ ነው የተባለው ግፍ እና መከራ እንዲቆም ነው፡፡
የትግራይ የሃይማኖት አባቶች እና ሊቃውንት ተመካክረዉ አሳልፈውታል የተባለውን ውሳኔ በኦርቶዶክስ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የመቐለ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢሳያስ ይፋ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡
በክልሉ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መገባደጃ በተመሳሳይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እንዲቆምና ሰላም እንዲወርድ በማለት ‹‹ጾመ ትግራይ›› የተሰኘ የጾም እና የጸሎት መርሐ ግብር መካሄዱ አይዘነጋም፡፡
አንድ ዓመት የተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት፣ በትግራይ ክልል የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡