Friday, November 29, 2024
spot_img

መንግሥት የአገር መከላከያ ሠራዊት ነፃ ያወጣቸውን ቦታዎች ይዞ ከመቆየት ውጪ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ ወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ታኅሣሥ 14፣ 2014 ― የመከላከያ ሠራዊት ከሕወሓት ኃይሎች ነፃ ያወጣቸውን ቦታዎች ይዞ እንዲፀና መወሰኑን መንግሥት አስታውቋል።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የመጀመሪያው ምዕራፍ በስኬት ተጠናቋል ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊት በአማራ እና አፋር አካባቢዎች ወራሪውን ኃይል በማፅዳት አሁን የያዘውን አካባቢዎች ይዞ እንዲቆይ መንግሥት መወሰኑን ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

መንግሥት ለዚህ ውሳኔ የደረሰው በተለያዩ ምክንያቶች እንደሆነ ነው ያመለከቱት።

በዚህም ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ያጋጠመውን ችግር ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አንስተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img