Friday, November 29, 2024
spot_img

ሐምዶክ ሥልጣን የመልቀቁን ነገር ትቼዋለሁ ማለታቸው ተሰማ

  • ከጦሩ መሪ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን መነጋገራቸው ተሰምቷል

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 13 2014 ― በትላናትናው እለት በሰዓታት ውስጥ ሥልጣናቸውን ሊለቁ መሆኑ ተነግሮ የነበረው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ሥልጣን የመልቀቁን ነገር ትቼዋለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የሳዑዲ ጋዜጣ እንደዘገበው ውሳኔያቸውን ያጠፉት ከአገሪቱ ጦር መሪ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታ አል ቡርሃን ጋር መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በትላናትናው እለት በሐምዶክ ዙሪያ ዘገባ ያስነበበው ሬውተርስ የዜና ወኪል በቅርቡ በመፈንቅለ መንግስት ከሥልጣናቸው ተወግደው ዳግም የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣቸውን ሊለቁ መሆኑን ለሚቀርቧቸው ጥቂት ፖለቲከኞች እና ምሁራን ተናግረዋል ብሎ ነበር፡፡

በመስከረም ወር መገባደጃ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን በሚመሩት የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ተወግደው የነበሩት ሐምዶክ፣ እንደገና ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት ከወር በፊት እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ሐምዶክ ወደ ሥልጣን ሲመለሱ ከጦሩ ጋር ስምምነት ፈርመው የነበረ ቢሆንም፣ ይህን ስምምነት ሱዳናዊያን እና የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ከጦሩ ጋር የፈረሙትን አዲስ የሽግግር ስምምነት በጽኑ እየተቃወሙት ይገኛሉ።

ሱዳን አሁንም የአደባባይ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች የምትገኝ ሲሆን፣ ባሳለፍነው እሑድ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የአገሩ ዜጎች አደባባይ ውለዋል፡፡ በካርቱም ውስጥ በተደረገው ሰልፍ ተቃዋሚዎች የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ የሆኑት የጄነራል ዐብደልፈታህ አል ቡርሃን መቀመጫ ወደሆነው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት አቅንተው ‹‹ሕዝቡ ጠንካራ ነው፣ ማፈግፈግ የለም›› በማለት ቡርሃን ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img