Friday, November 29, 2024
spot_img

መቼቱን ሐረር ያደረገው ‹‹ፈያ ዳኢ›› ዘጋቢ ፊልም ለኦስካር ሽልማት ታጨ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 13፣ 2014 ― በኢትዮጵያዊ ሜክሲኳዊቷ ጀሲካ በሽር የተሠራውና መቼቱን ሐረር ያደረገው ‹‹ፈያ ዳኢ›› የተሰኘ ርእስ ያለው ዘጋቢ ፊልም ለኦስካር ሽልማት ታጭቷል፡፡

ኦስካር ትላንት ለ94ኛ ጊዜ ለሚያዘጋጀው ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚያወዳድራቸውን ፊልሞች ይፋ ሲያደርግ የጀሲካ ፊልም መታጨቱ ታውቋል፡፡

አሁን ለኦስካር የታጨውን ዘጋቢ ፊልም ያዘጋጀችው ጀሲካ በሽር የተወለደችው ሜክሲኮ ሲቲ ሲሆን፣ ያደገችው ደግሞ ሐረር ነው፡፡

በፈረንጆቹ በ1987 ቤተሰቧ ከኢትዮጵያ ሲሰደድ የ16 ዓመት እድሜ የነበራት ጄሲካ፣ ከሁለት ዐስርት ዓመታት የስደት ሕይወት በኋላ በእድሜ የገፉትን አያቷን ልትጠይቅ አገር ቤት በተመለሰችበት ወቅት ዘጋቢ ፊልሙ እንደተጸነሰ ነው ለቢቢሲ የተናገረችው፡፡
የዩሲኤልኤ የፊልም ምሩቅ የሆነችው ፕሮዲውሰር እና ሲኒማቶግራፈሯ ጀሲካ፣ የምትኖረው ኒው ዮርክ ሲሆን፣ ‹‹ፈያ ዳኢ››ን ለማጠናቀቅ 10 ዓመታት እንደፈጀባት ተናግራለች፡፡

ሁለት ሰዓት ገደማ የሚወስደው ‹‹ፈያ ዳኢ›› ለዕይታ የበቃው አምና ነው። በፊልሙ ዓለም ገናና ሥም ያላቸው ሰንዳንስ እና ትሩ/ፎልስ ፌስቲቫሎችን ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ታይቷል።

የፊልም ሐያሲዎች እና ፊልም ሠሪዎችን ጨምሮ የፊልሙን ማኅበረሰብ ላነጋገው ፈያ ዳኢ፣ ዘ ኢኮኖሚስት፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ቮግ፣ ቫራይቲ እንዲሁም ሌሎችም መገናኛ ብዙኃን ስለ ዳሰሳ በማስነበብ በዓመቱ መታየት ካለባቸው ፊልሞች ዝርዝር ውስጥ አካተውታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img