Sunday, November 24, 2024
spot_img

አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር ተለቀቁ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 12፣ 2014 ― የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ አመራሩ አቶ አብርሃ ደስታ ከእስር መለቀቃቸውን ገልፀዋል።

82 ቀናት በእስር እንዳሳለፉ የገለጹት አቶ አብርሃ ደስታ፣ በአስር ሺሕ ብር ዋስትና መለቀቃቸውን ነው ያስታወቁት።

ለጥቂት ወራት ትግራይ ክልልን ባስተዳደረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዋና ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ አብርሃ ደስታ አዲስ አበባ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

የአረና አመራሩ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በነበሩት ባለፉት ሁለት ቀናት ‹‹ትግርኛ መናገር እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የትግራይ ተወላጆች ያለ ሀጥያታቸው ፍርድ ቤት ሳያውቃቸው ከያሉበት እየታፈሱ እየታሰሩ ›› ነው የሚል እንዲሁም የጦርነቱን አስከፊነት የሚገልጹ ጹቁጥጥር ስር የመዋላቸው ዜና ከመሰማቱ ከሰዓታት በፊት ደግሞ ‹‹ጦርነትን መደገፍ ባህል ሲሆን ስለ ሰላም መስበክ ነውር ይሆናል። ፀብ ካሸለመ ዕርቅ ያስነውራል። ስለ ሰላም የሚዘረጉ እጆች የተቀደሱ ናቸው። ሰላም ለሕዝባችን›› የሚል ጽሑፍ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍረው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img