Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሕወሓት ቃል አቀባዩ የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬትስ ለመንግሥት ድሮን ታቀርባለች በሚል ከሰሱ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ታኅሣሥ 12፣ 2014 ― የሕወሓት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ የተባበሩት ዐረብ ኤሜሬት ለመንግስት ድሮን ታቀርባለች በሚል ክስ አዘል ወቀሳ አቅርበዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው ሲሉ ወንጅለዋል፡፡

ጦርነቱ ሲጀመርም የኤምሬትስ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በህወሓት መሳሪያዎች ላይ ጥቃት እንዳደረሱ የተናገሩት ቃል አቀባዩ፣ ይህም ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ የአሸናፊነት ሚዛኑን አስጠብቋል ብለዋል።

‹‹ድሮን ለኢትዮጵያ በመስጠት ሌሎች አገራት እንዳሉ መረጃዎችን ያመላክታሉ›› የሚሉት አቶ ጌታቸው፣ ከነዚህም ውስጥ ቻይና ሚሳኤልና ድሮን በመሸጥና በማቅረብ እንዲሁም ኢራንንም ጠቅሰዋል፡፡  

ከዚሁ ጋር አያይዘውም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ ክልል ላይ የተዋጊ አውሮፕላን በረራ እገዳን ጨምሮ ሌሎች ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በጦርነቱ ተሳታፊ ያሏቸው ወገኖች እየጨመሩና ጦርነቱም ቀጣናዊ መልክ መያዙን የጠቆሙ ሲሆን፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ድሮኖች ሰላማዊ ሰዎችን እያጠቁ ነው ቢሉም መንግሥት የአገር መከላከያ ሠራዊት የሚፈጽመው የአየር ጥቃት ኢላማ የሚያደርገው የሕወሓት የማሰልጠኛ ቦታ ወይም የጦር መሳሪያ መከማቻ መሆኑን ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img