Sunday, July 7, 2024
spot_img

በዛሬው እለት የሚሠበሠበው የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ጉዳይ በተደራቢ አጀንዳነት እንደሚመለከተው ተነገረ

  • የኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲካተት በስብሰባው የጠየቁት አሜሪካ እና አየርላንድን ጨምሮ 6 አገራት ናቸው

(አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 11 2014) ― ዛሬ ሰኞ ታኅሣሥ 11፣ 2014 የሚሠበሠበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ጉዳይ በተደራቢ አጀንዳነት ይመለከተዋል ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ የሚነሳው የኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረቱን የሚያደርገው በሰብአዊ እርዳታ ጉዳይ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በስብብባው ማጠቃለያ ላይ እንደ ተጨማሪ አጀንዳ ይነሳል የተባለውን የኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲካተት የጠየቁት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ ናቸው፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ትግራይ ውስጥ ከተቀሰቀሰ በኋላ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከ10 ጊዜ በላይ መወያየቱ አይዘነጋም፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት በትግራይ ጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር በተስፋፋው ጦርነት ምክንያት 9 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img